ኮሮናቫይረስ በዓለም ጤና ድርጅት ረቡዕ በይፋ “ወረርሽኝ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በአልበርታ አጠቃላይ የተረጋገጡ ጉዳዮች ቁጥር ወደ 19 ከፍ ማለቱን የክልሉ ከፍተኛ ዶክተር ገለጹ።

ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ዲና ሂንሻው በአልበርታ አምስት አዲስ የተገኙ ሲሆን ከዚህ ሦስቱ  በካልጋሪ ዞን መሆኑን አስታወቁ።

ዶ/ር ሂንሻው በበኩላቸው የበሽታው መስፋፋት በአልበርታ እና በዓለም ዙሪያ እንደሚቀጥል ጠቁሟል።

የበሽታ ባለሙያዎች “ወረርሽኝ” የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት  በሽታው በብዙ አገሮች እና አህጉሮች በአንድ ጊዜ ወረራው በሚያስፋፋበት ጊዜ ነው። ይህም ሕመሙ ምን ያህል የተስፋፋ እንደሆነ ይገልጻል።

በክልሉ ውስጥ ሁሉም የተረጋገጡ ጉዳዮች ከጉዞ ጋር የተዛመዱ ናቸው።

አውራጃው ወዲያውኑ ተፈጻሚ የሚሆን በቅርቡ ከጣሊያን የተመለሱ ተጓዞችን ለ 14 ቀናት ራሳቸውን እንዲገለሉ ጠይቋል;;

ዶ/ር ሂንሻው ክልሉ በቅርቡ ከካናዳ ውጭ ከየትኛውም ቦታ የተመለሱ ተጓዞች በሙሉ በትላልቅ የህዝብ ስብሰባዎች ላይ መገኘታቸውን ለመገደብ እና እንደ ትኩሳት ወይም ሳል ያሉ ምልክቶችን ለመከታተል እንዲያስቡ ይመክራል ብለዋል።

ዕድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ የሆኑ እና ሥር የሰደደ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ከካናዳ ውጭ ላለመጓዝ እንደሚመከሩ ዶ/ር ሂንሻው ገለፁ። “በአሁኑ ወቅት ብዙ የአልበርታ ነዋሪዎች በሚገኘው መረጃ እንደሚጨነቁ አውቃለሁ።

“ሁሉም የአልበርታ ነዋሪዎች እየተከሰተ ስላለው ነገር አስተማማኝ መረጃ እንዲያገኙ እና የውሸት ወሬዎችን እና ትክክል ያልሆኑ መረጃዎችን መስፋፋትን ለማስቆም የበኩላቸውን እንዲወጡ ማበረታታት እፈልጋለሁ።

ኮቪድ -19 የጤና ስርዓታችንን እና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነታችንን ሊፈትሽ ነው ነገር ግን ስርዓታችን ለዚያ ፈተና እየተዘጋጀ ነው።

 

አምስት አዳዲስ ጉዳዮች ተረጋግጠዋል

ረቡዕ ከተረጋገጠው አዲስ ጉዳይ  መካከል አንድ ሰው በ 20 ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኝ ከካልጋሪ አካባቢ ነው። ከካልጋሪ ዞን በ 30 ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሁለት ሴቶችም ለቫይረሱ እንደተጋለጡ ምርመራ ኣሳይተዋል።

በአዲሱ ጉዳዮች መካከል በኢድሞንቶን በ 30 ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ እና በማዕከላዊ ዞን 30 ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ሴት ናቸው;;

አምስቱ ሰዎች በቅርቡ ከኢራን ፣ ከግብፅን ፣ ከስፔን ፣ ከሜክሲኮን እና ከአሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አገሮችን ከመጎብኘት የተመለሱ ናችው።